የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሙስጠፌ መሃመድ ከጀረር ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያዩ

By Alemayehu Geremew

May 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 4፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሃመድ ከጀረር ዞን ነዋሪዎች ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይት መድረኩ በሕዝቡ የመሰረተ ልማት ጥያቄዎች፣ በምርትና ምርታማነት ማሳደግ፣ በሰላምና ጸጥታ እንዲሁም በልዩ ኃይል መልሶ ማደራጀት ዙሪያ ምክክር ተደርጓል፡፡

አቶ ሙስጠፌ÷ ሰሞኑን በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች በተለይ በወንዞችና ተፋሰስ አከባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ዜጎች እየተደረገ ያለውን ድጋፍ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም የክልሉ መንግሥት ከሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ከአየር ኃይልና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመተባበር ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም አስረድተዋል።

በርዕሰ መስተዳደሩ የተመራ ከፍተኛ የክልሉ ባለስልጣናት በቀጣይም ከሌሎች የሕበረተሰብ ክፍሎች ጋር እንደሚወያይ የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡