አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የአቅመ ደካሞች እና ችግር ላይ ያሉ ወገኖች ቤት እድሳት ላይ ሁሉም እንዲሳተፍ ጥሪ አቀረቡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው አዋሬ አካባቢ የሚኖሩ አቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ዓመታዊ መርሐ ግብርን አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ባለፉት ሳምንታት ያየነው ከባድ ዝናብ ሁላችንም ለተቸገሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እጃችንን እንድንዘረጋ ሊያስተምረን ይገባል ብለዋል።
“ሁላችንም በዚህ ዓመታዊ ጥረት እንድንተባበር ጥሪየን አቀርባለሁ” ብለዋል በመልዕክታቸው።