የሀገር ውስጥ ዜና

የምርምር ተቋማትን ከኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

By Tamrat Bishaw

May 13, 2023

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 5 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የትምህርት እና የምርምር ተቋማትን ከኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰር እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

“የዩኒቨርሲቲ እና ኢንዱስትሪዎች ትስስር ለተግባር ተኮር መማር ማስተማርና ምርምር” በሚል መሪ ቃል የምክክር መድረክ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ነው።

በመድረኩ የተገኙት የትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ሳሙኤል ክፍሌ (ዶ/ር)÷ ዩኒቨርሲቲዎች የትምህርት ጥራትና ተገቢነት ላይ ትኩረት በማድረግ ችግር ፈቺ የትብብር ምርምር ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል።

ኢንዱስትሪዎችም ለዩኒቨርሲቲዎች ሃብት በመፍጠርና የጋራ ፕሮጀክትን በመተግበር ለጋራ ተጠቃሚነት እንዲሰሩ አሳስበዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ንጉስ ታደሰ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷የተግባር ትምህርትን ከኢንዱስትሪዎች ጋር ለማስተሳሰርና ምርምሮች በኢንዱስትሪዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ እንዲሆኑ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በሳምራዊት የስጋት