አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 15፣ 2012(ኤፍ ቢ ሲ) 71ኛው የኢጋድ አስቸኳይ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በቪዲዮ ኮንፈረንስ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
የዛሬው የቪዲዮ ኮንፈረንሰ የኢጋድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር የሆኑት የሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አስማ አብደላህ እና የኢጋድ ዋና ጸሀፊ ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በይፋ ተከፍቷል።
የቪዲዮ ኮንፈረንሱ በዋናነት በደቡብ ሱዳን የተከሰተውን ግጭት ለማስቆም የተደረሰው ስምምነት ያለበትን ደረጃ በመገምገም ውሳኔዎችን ለማሳለፍ ያለመ ነው።
በቪዲዮ ኮንፈረንሱ የኢጋድ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።