አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም ለ24ኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ2ኛ ጊዜ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከል ቀንን ተከበረ።
የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ቀኑን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው መልዕክታቸውን አስፍረዋል፡፡
በዚህም ÷ባለፉት ሁለት ዓመታት ለእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከል ትኩረት በመስጠት አደጋ መከላከል የሚያስችል ዘመናዊ ተቋም ፣ የሰው ኃይልና አሰራር እንዲኖር ተቋሙ ከከተማዋ ዕድገት ጋር አብሮ በሚሄድ ዘመናዊ ግብዓት እንዲጠናከር ትኩረት ሰጥተን ሰርተናል ብለዋል፡፡
“የአደጋ መከላከል ሰራተኞች ፣ አደጋ ለመከላከል አደጋ ውስጥ የምትገቡ ፣ የሌላውን ሕይወት ለማትረፍ የራሳችሁን ሕይወት የምትሰጡ ናችሁና ክብር ይገባችኋል” ሲሉም ነው የገለጹት።
ኅብረተሰቡም የእሳት አደጋ በመከላከል ረገድ የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡
አደጋዎች ሲደርሱም የከፋ ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት ጥቆማዎችን በፍጥነት በመስጠት የበኩሉን አስተዋፅዖም እንዲያበረክት ጨምረው አሳስበዋል::