አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር የበለጸገው የመረጃ ሥርዓት የውጭ ሀገራት ሥራ ሥምሪት ላይ ያሉ ክፍተቶችን ለመሙላት ጉልኅ ሚና ይኖረዋል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሥራና ክኅሎት ሚኒስቴር በልጽጎ ሥራ ላይ የዋለውን የውጭ ሀገር የሥራ ሥምሪት መረጃ ሥርዓት ጎብኝተዋል፡፡
ሥርዓቱ የዜጎችን የመረጃ አያያዝ ዘመናዊ በማድረግ በዜጎች ላይ ይደርሱ የነበሩ ችግሮችን ያስቀራል ሲሉም በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ጠቁመዋል።