የሀገር ውስጥ ዜና

የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ

By Alemayehu Geremew

May 14, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 6፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በጣሊያን ሮም ከተማ በድንገት ሕይወቱ ያለፈው የክላርኔት የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቹ የአርቲስት ዳዊት ፍሬው የቀብር ሥነ-ሥርዓት ተፈፀመ።

በሀገር ፍቅር ቲዓትር ቤት የሙያ አጋሮቹ  የሽኝት ሥነ-ሥርዓት ከተከናወነ በኋላ በመንበረ ፀባኦት ቅድስ ሥላሴ ካቴድራል የቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ተፈፅሟል፡፡

በቀብር ሥነ-ሥርዓቱ ላይ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ አርቲስቶች፣ የአርቲስቱ ወዳጆች እና ቤተሰቦች ተገኝተዋል።

በምንተስኖት ሙሉጌታ