የሀገር ውስጥ ዜና

በአትላንታ ከተማ ከንቲባ የተመራ ልዑክ  የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎበኘ

By Mikias Ayele

May 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአትላንታ ከተማ ከንቲባ አንድሬ ዲከንስ የተመራ የልዑካን ቡድን የኢትዮጵያ አየር መንገድን ጎብኝቷል፡፡

የልዑካን ቡድኑ አባላት የአየር መንገዱን የስራ እንቅስቃሴና  ዘመናዊ ክፍሎችን ተዘዋውረው መመልከታቸውን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ልዑኩ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን  ጣሰው እና ሌሎች  ከፍተኛ  አመራሮች  ጋር  በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መወያየቱም ተጠቁሟል፡፡