አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአርሶ አደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን ያዘጋጀው የሌማት ትሩፋት አውደ ርዕይ መካሄድ ጀመረ፡፡
“ምግባችን ከደጃችን” በሚል መሪ ሀሳብ በሳይንስ ሙዚየም እየተካሄደ ባለው በዚሁ አውደ ርዕይ ማር፣ ዶሮ፣ እንቁላል አትክልትና ፍራፍሬን ጨምሮ የተለያዩ የግብርና ውጤቶች ለዕይታ ቀርበዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ስራ አስኪያጅ አቶ ጥራቱ በየነ አውደ ርዕዩን መጎብኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
አቶ ጥራቱ ከዚህ በተጨማሪ በግብርና ሚኒስቴር እና ባለድርሻ አካላት ተዘጋጅቶ ከዚህ ቀደም የተከፈተውን የግብርና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎብኝተዋል፡፡