የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ የዱባይ ዓለም አቀፍ ምክር ቤት የመካከለኛው ምስራቅና የአፍሪካ ኃላፊ ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

May 16, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ የዱባይ ዓለም አቀፍ ምክር ቤት የመካከለኛው ምስራቅና የአፍሪካ ኃላፊ ከሆኑት ካሊድ አል አሊ ጋር በዱባይ ተወያይተዋል፡፡

በውይይቱ ÷ ከቀጠናው አዲስ ኢንቨስትመንቶችን መሳብ ስለሚቻልባቸው ስትራቴጂካዊ መንገዶችና የኢንቨስትመንት አጋርነቶች እንዲሁም የጋራ ፕሮሞሽን ስራዎች ዙሪያ መምከራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡