የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ የሚያደርገውን አዲስ በረራ ጀመረ

By Meseret Awoke

May 16, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አሜሪካ አትላንታ የሚያደርገውን አዲስ በረራ ዛሬ መጀመሩን አስታወቀ።

የበረራው ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በስካይላይት ሆቴል ተካሂዷል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ትሬሲ ጃኮብሰን፣ የአትላንታ ከንቲባ አንድሪው ዲክንስ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ግርማ ዋቄ፣ የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው፣ የአየር ኃይል ዋና አዛዥ ሜጀር ጄነራል ይልማ መርዳሳ እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አትላንታ ዛሬ የሚጀምረው በረራ በአሜሪካ ያሉትን መዳረሻዎች ቁጥር ወደ ስድስት ያሳድገዋል።