የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኒንዢያ ግዛት የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ ፀሐፊ ጋር መከሩ

By Alemayehu Geremew

May 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሠ-መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በኒንዢያ ግዛት የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ፀሐፊ ሊያንግ ያንሹን ጋር ተወያዩ።

በኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ፅኅፈት ቤት በተካሄደው ውይይት በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋንን ጨምሮ የተለያዩ አካላት ተገኝተዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች በባሕል፣ በቋንቋና በምጣኔ ሐብት ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከኦሮሚያ ርዕሰ መስተዳድር ጽኅፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አቶ ሽመልስ ፥ ኢትዮጵያ የምታካሂደውን የልማት ሥራ ለማፋጠን እና ምጣኔ ሐብቷን ለማሳደግ “የቤልት ኤንድ ሮድ ኢኒሼቲቭ” ሚና ከፍተኛ እንደሆነ አንስተውላቸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ኢኒሼቲቩን ዕውን በማድረግ ረገድ የቻይናን ጠንካራ ድጋፍ ትፈልጋለችም ነው ያሉት፡፡