የሀገር ውስጥ ዜና

ጀርመን ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር እንደምትፈልግ አስታወቀች

By Meseret Awoke

May 18, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጀርመን ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስታይንማየር ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር እንደምትፈልግ ገለጹ፡፡

በጀርመን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት አምባሳደር ፍቃዱ በየነ ለጀርመን ፌዴራል ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፍራንክ ዋልተር ስቴንሚር የሹመት ደብዳቤያቸውን አቅርበዋል፡፡

የሹመት ደብዳቤያቸውን ሲያቀርቡ በፌዴራል ፕሬዚዳንቱ ጽህፈት ቤት በተከናወነ ደማቅ ሥነ-ሥርዓት እንደሆነ ተጠቅሷል፡፡

አምባሳደር ፍቃዱ ከፕሬዝዳንቱ ጋር በነበራቸው ውይይት ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።

ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከርና ያላቸውን ፍላጎት ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ በጀርመን ሀገር በሚኖራቸው ቆይታ አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ እንደሚያደርጉላቸውም ቃል ገብተዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!