አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ከዓለም የምግብ ፕሮግራም ልዑክ ጋር ተወያዩ፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ ከዓለም ምግብ ፕሮግራም በስነ-ምግብ ዘርፍ ዋና ዳይሬክተር የተመራ የድርጅቱ ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ልዑክን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
በውይይታቸውም ድርጅቱ በክልሉ አካባቢዎች እያከናወናቸው ያሉ ስራዎችን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መክረው ከመግባባት ላይ መድረሳቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽ መረጃ ያመላክታል፡፡