የሀገር ውስጥ ዜና

የአማራ ክልል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች የግብርና እና ሳይንስ አውደ ርዕይን ጎበኙ

By Amele Demsew

May 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እና የግብርና ባለሙያዎች በሳይንስ ሙዚየም በመገኘት በግብርና ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የግብርና እና ሳይንስ አውደ ርዕይ ጎብኝተዋል።

ዐውደ ርዕዩ ፥ የቴክኖሎጂ ዕውቀትን ለማሸጋገርና እና ምርታማነትን ለማሳደግ ትልቅ ተሞክሮ የሚወሰድበት መሆኑን የጉብኝቱ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ግብርናን በቴክኖሎጂ በማዘመን ምርታማነትን ለማሳደግ ትኩረት ሊሠራ እንደሚገባም መገለጹን የዘገበው አሚኮ ነው፡፡