የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤልና ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፎረንሲክ ኢንስቲትዩትን ጎበኙ

By Shambel Mihret

May 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገብረሚካኤል እና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ እያስገነባ የሚገኘውን የፎረንሲክ ኢንስቲትዩት ጎብኝተዋል።

በዩኒቨርሲቲው የሚገነቡ መሰረተ ልማቶችንና ሠልጣኝ መኮንኖችን የተመለከቱት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎቹ÷ በዩኒቨርሲቲው ለሚገነባው ዓለም አቀፍ የፖሊስ አመመራር ኢንስቲትዩት የግንባታ ስራን አስጀምረዋል።

የሚገነባው ኢንስቲትዩት  በለስድስት ወለል ሲሆን÷ካፍቴሪያን ጨምሮ የስብሰባ አዳራሾች እና  ለተለያዩ አገልግሎቶች መስጫ ማዕከላትን ያካተተ ነው ተብሏል።

በጉብኝቱ ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሽመልስ አብዲሳ እና ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች ተገኝተዋል።

በወንድሙ አዱኛ