የሀገር ውስጥ ዜና

240 ሺህ ለሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ሊሠጥ ነው

By Alemayehu Geremew

May 23, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 15፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 240 ሺህ ለሚደርሱ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች በበይነ-መረብ የመውጫ ፈተና ለመሥጠት መዘጋጀቱን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንደገለጹት ÷ በ2015 ዓ.ም በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለሚመረቁ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ለመሥጠት ብሉ -ፕሪንት ተዘጋጅቷል፡፡

የመውጫ ፈተና የክፍያ ተመን ረቂቅ መመሪያ መዘጋጀቱንም ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረቡት ሪፖርት አብራርተዋል፡፡

የመውጫ ፈተና ስትራቴጂ ማስፈፀሚያ መመሪያ እና የድርጊት መርሐ-ግብር ዝግጅት መጠናቀቁንም ነው የገለጹት፡፡

በመውጫ ፈተና የሚካተቱ የትምህርት ዓይነቶች ተለይተው በቅድመ-ምረቃ በሚሰጡ በሁሉም የትምህርት መስኮች የፈተና ንድፍ ማሳያ መዘጋጀቱን ማስረዳታቸውንም የምክር ቤቱ መረጃ ያመለክታል፡፡