የሀገር ውስጥ ዜና

ከንቲባ አዳነች ከኮሎራዶ የጥቁር ሴቶች የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፕሬዚዳንት ጋር ተወያዩ

By Feven Bishaw

May 25, 2023

 

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ዴንቨር በነበራቸው ቆይታ ከኮሎራዶ የጥቁር ሴቶች የፖለቲካ እንቅስቃሴ ፕሬዚዳንት ቢያንካ ኤመርሰን ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸው÷ የሴቶች የፖለቲካ ተሳትፎን ማሳደግ እና ማብቃት ላይ በትብብር መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን ከንቲባዋ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው አስፍረዋል፡፡