የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ”ሽልማት አሸነፈ

By Alemayehu Geremew

May 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በዓመታዊው የ“አፔክስ” የመንገደኞች ምርጫ “ምርጥ የአፍሪካ አየር መንገድ” ሽልማት አሸንፏል፡፡

አየር መንገዱ ሽልማቱን የተቀዳጀው በምርጥ የበረራ መስተንግዶ፣ መዝናኛ ፣ ምግብና መጠጥ፣ ምቾት እንዲሁም በገመድ ዓልባ የኢንተርኔት “ዋይ ፋይ”አገልግሎት ዘርፎች መሆኑን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።

አየር መንገዱ ሽልማቱን የተቀበለው በአየርላንዷ ደብሊን በተዘጋጀ መርሐ-ግብር ነው፡፡