የሀገር ውስጥ ዜና

ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By Meseret Awoke

May 25, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ጋር ተወያይተዋል።

ይልቃል ከፋለ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው እንዳሉት፥ ኢትዮጵያና ቻይና ረጅም ዘመናትን ያስቆጠረ ጠንካራ የትብብር ግንኙነት ያላቸው ሀገራት ናቸው።

“በአማራ ክልልም በትምህርትና ስልጠና፣ በቴክኖሎጂ ትውውቅና በተለያዩ የትብብር መስኮች በጋራ ለመስራት የጀመርነውን ግንኙነቶች ይበልጥ አጠናክረን እንቀጥላለን” ብለዋል።

የአማራ ክልል የበርካታ ጸጋዎች ባለቤት ነው ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ ፥ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለሚፈልጉ የቻይና ባለሃብቶች አስፈላጊው ድጋፍ እንደሚደረግም አረጋግጠዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!