የሀገር ውስጥ ዜና

በዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ አውደ-ርዕይ ላይ የሚደረግ ተሳትፎን ማሳደግ ያስፈልጋል- በለጠ ሞላ (ዶ/ር)

By Mikias Ayele

May 26, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ አውደ-ርዕይ ላይ የሚደረግ ተሳትፎን ማጠናከርና ማሳደግ ያስፈልጋል ሲሉ የኤኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር  በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ተናገሩ፡፡

በሞሮኮ በሚካሄደው ዓለም አቀፍ የቴክኖሎጂ አውደ-ርዕይ ላይ የሚሳተፉ ስምንት የኢትዮጵያ ስታርትአፖችና አይሲቲ ቢዝነሶች ሽኝት ተደረገላቸው።

ስታርት አፕ ድርጅቶቹ የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ባወጣው ውድድር  የተመረጡ ሲሆኑ÷ በጃፓን ዓለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ድጋፍ እና ስፖንሰር ተደርገዋል።

እነዚህ ስታርትአፖች እና የአይሲቲ ቢዝነሶች ኢትዮጵያን በመወከል በዓለም አቀፉ የቴክኖሎጂ አውደ-ርዕይ ላይ የሚሳተፉ ሲሆን÷ በኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሽኝት ተደርጎላቸዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የኤኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)÷ የኢትዮጵያን ተሞክሮ በአለምአቀፉ የቴክኖሎጂ አወደ ርዕይ ለማሳየት የተፈጠረው እድል  መልካም የሚባል ጅምር  ነው ብለዋል፡፡

በቀጣይም እንዲህ ያሉ ተሳትፎችን በይበልጥ ማጠናከርና ማስፋት ያስፈልጋል ማለታቸውን ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡