የሀገር ውስጥ ዜና

ጣሊያን ለኢትዮጵያ የ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ ድጋፍ አደረገች

By Alemayehu Geremew

May 31, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጣሊያን በኢትዮጵያ ለመልሶ ግንባታ ስራዎች የሚውል የ7 ነጥብ 6 ሚሊየን ዩሮ

ድጋፍ አድርጋለች፡፡

ድጋፉ በአፋር እና ደቡብ  ክልሎች በጤና፣ ትምህርትና የንጹሕ  መጠጥ ውሃ አቅርቦት ላይ የሚሠሩ የመልሶ ግንባታሥራዎችን እና መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻል እንደሚውል ተገልጿል፡፡

አምባሳደር አጎስቲኖ ÷የጣሊያን መንግስት በኢትዮጵያ ጉዳት  የደረሰባቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች መደገፍ  በመቻሉ እንደተደሰቱ  መናገራቸውን በኢትዮጵያ የተመድ ፕሮጀክቶች ማስተባበሪያ ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡