የሀገር ውስጥ ዜና

ከ148 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባድ እቃዎች ተያዙ

By Mikias Ayele

June 02, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ148 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባድ እቃዎች በድሬዳዋ ግምሩክ ቅርንጫፍ መያዛቸውን የግምሩክ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች÷ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክ ፣ የመኪና መለዋወጫ፣ የመዋቢያ እቃዎች፣ መድሃኒቶች፣ የምግብ ነክ እቃዎች እና የቤት ውስጥ መገልገያ እቃዎች ናቸው፡፡

እቃዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ መሰረት የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፣ የፌደራል ፖሊስ እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራኞች በጋራ ባደረጉት ክትትል መሆኑን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የኮንትሮባንድ አዘዋዋሪዎቹ በፀረ ኮንትሮባንድ ግብረኃይሉ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ሲያውቁ ተሽከርካሪዎቹን ወደ ጫካ በማስገባት ለመሰወር ቢሞክሩም የተሰማራው ግብረ ሀይል በቁጥጥር ስር ማዋል መቻሉ ተገልፃል።