አዲስ አበባ፣ ግንቦት 26፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር በሞሮኮ እየተጋጀ ባለዉ የጂአይቴክስ አፍሪካ ኢትዮጵያን ወክለዉ የተገኙ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችን ጎበኙ፡፡
በሞሮኮ ማረከሽ በአፍሪካ ለመጀምሪያ ጊዜ በተካሄደዉ ኮንፈረንስ ላይ ‘‘የአቅም ግንባታ ስራ ለሙያዊ ልህቀትና ኢኮኖሚ ልማት’’ በሚል መድረክ ላይ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተር ሰለሞን ሶካ ተካፍለዋል፡፡
ከመድረኩ ጎን ለጎን ጀማሪ ኢትዮጵያውያን ስራ ፈጣሪዎችን ጎብኝተዋል።
ኮንፈረንሱ ትኩረቱን በሳይበር ደህንነት፣ በክላዉድ ኮምፒዉቲንግ ፣ በአርተፍሻል ኢንተለጀንስ፣ በፊንቴክ ፣ በዲጂታል ከተማ፣ አግሪ ቴክ መሰል የቴክኖሎጂ ዘርፎች አድርጓል ነው የተባለው፡፡
በዚህ መርሐ ግብር ላይም ኢትዮጵያ ምርትና አገልግሎቶቿን እያስተዋወቀች እንደምትገኝ ተጠቁሟል፡፡
በጉብኝቱ ወቅት በሳይበርና መሰል ጉዳዮች ላይ አቅም ያላቸዉ አካላት ኢመደአ በትብብር ሊሰሩ እንደሚገባና ተቋሙ በትብብር ለመስራት ዝግጁ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ አንስተዋል።
በጉብኝቱ የኢመደአ ዋና ዳይሬክተርን ጨምሮ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) ተሳትፈዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!