የሀገር ውስጥ ዜና

የብራዚሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ነገ አዲስ አበባ ይገባሉ

By Amele Demsew

June 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ማውሮ ቪዬራ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በነገው ዕለት አዲስ አበባ እንደሚገቡ በኢትዮጵያ የብራዚል አምባሳደር ጃንዲር ፌሬራ ዶስ ሳንቶስ ገልጸዋል፡፡

በጉብኝቱ የአፍሪካ እና የመካከለኛው ምስራቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ካርሎስ ዱዋርቴም ከልዑካን ቡድኑ ጋር እንደሚመጡ ታውቋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን እንዲሁም የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳፋኪ መሃመት ጋር ይገናኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በጉብኝታቸው ብራዚል ከኢትዮጵያ እና ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ያላትን አጋርነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ መባሉን ኢፕድ ዘግቧል፡፡