የሀገር ውስጥ ዜና

የኢትዮጵያና ቻይና የባህልና ቋንቋ ልውውጥ ለአገራቱ ግንኙነት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ አለው – አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን

By Amele Demsew

June 04, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያና የቻይና የባህልና ቋንቋ ልውውጥ ለሀገራቱ ግንኙነት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን ገለጹ።

በኢትዮጵያ የቻይና ቋንቋ ችሎታን ለማሻሻል በዩንቨርሲቲ ደረጃ ከሚያጠኑ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ተማሪዎች በቻይንኛ ቋንቋ የተለያዩ የመድረክ ሥራዎችን አቅርበዋል።

በመድረኩ ተማሪዎቹ በቻይንኛ ቋንቋ ንግግሮች፣ ሙዚቃና ስፖርት እንዲሁም ልዩ ልዩ ትዕይንቶችን አሳይተዋል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዣኦ ዥዩዋን በዚሁ ጊዜ እንዳሉት÷ የባህልና የቋንቋ ልውውጡ የሀገራቱን ማህበረሰብ ለመገንባት አስፈላጊ ነው ፡፡

ዓለም በተለያዬ ስልጣኔ የተዋቀረች መሆኗን ጠቅሰው÷ የኢትጵያና ቻይና ወጣቶች የተጣለባቸውን ታሪካዊ ሀላፊነት እንደሚወጡ እምነት አለኝ ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ቻይና በተለያዩ የትብብር መስኮች ያላቸው ግንኙነት እየተጠናከረ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ እና ቻይና የባህልና ቋንቋ ልውውጥ ለአገራቱ ግንኙነት መጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ጠቅሰዋል፡፡

አገራቱ ያላቸው አጋርነት በተለይም በኢኮኖሚ መስክ ወደ ላቀ ደረጃ እያደገ መምጣቱም ተገልጿል፡፡

በመድረኩ የቻይና ዲፕሎማቶች፣ የትምህርት ፣ የስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እንዲሁም የቱሪዝም እና የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስራ ሀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡