የሀገር ውስጥ ዜና

የቀቤና ብሔረሰብ የታሪክ፣ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም በወልቂጤ ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡

By Shambel Mihret

June 04, 2023

በ3ኛው የቀቤና ብሄረሰብ የታሪክ፣ የባህልና የቋንቋ ሲምፖዚየም ላይ በብሄረሰቡ ምሁራን የተዘጋጁ የተለያዩ የጥናትና ምርምር  ስራዎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው።

በዋናነት የቀቤና የፅሁፍ ቋንቋን ከሳባ ወደላቲን ለመቀየር የተጠና ጥናት ለውይይት የቀረበ ሲሆን÷ ተሳታፊዎች አስተያየት ሰጥተውበታል።

በዝግጅቱ ምሁራን፣ የብሔረሰቡ ተወላጆች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተሳትፈዋል፡፡

በምንተስኖት ሙሉጌታ