የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

June 05, 2023

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 28፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ከብራዚል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማውሮ ቪዬራ  ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረናል ብለዋል።

በኢትዮጵያ እና በብራዚል መካከል ግንኙነትን ስለማጠናከር እና በብዝኃ ወገን ጉዳዮች ላይ ውይይት እናደርጋለን ሲሉም ገልጸዋል፡፡