የሀገር ውስጥ ዜና

32ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው

By Melaku Gedif

June 09, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 32ኛው የጉሚ በለል የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡

የውይይት መድረኩ “ቃል እና ተግባር ከትውልድ እስከ ትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

በመድረኩ የመስኖ እና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር ዴኤታ ብርሃኑ ሌንጂሶ (ዶ/ር) እና የኦሮሚያ ክልል ኮሙኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ አቶ ሃይሉ አዱኛን ጨምሮ ተማሪዎች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል፡፡