አዲስ አበባ፣ ሰኔ 2፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የፖርቹጋል አምባሳደር ሉሲያ ፍራጎሶ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም የኢትዮጵያ እና የፖርቹጋልን የኢንቨስትመንት ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡
ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ የውጭ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን እንዲያፈሱ አስፈላጊው ትብብር እንደሚደረግ መናገራቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!