የሀገር ውስጥ ዜና

“የጋራ ተግዳሮቶቻችንን በድል ለመወጣት ኢትዮጵያ ከእያንዳንዱ ሀገር ጋር ተቀራርባ ትሠራለች” – ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ

By Alemayehu Geremew

June 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋራ ጥቅሞችን እና ሥጋቶችን ከግምት ውስጥ በማስገባት ተግዳሮቶችን በድል ለመወጣት ኢትዮጵያ ከእያንዳንዱ ሀገር ጋር ተቀራርባ እንደምትሠራ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ዛሬ ጠዋት ከሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሐሰን ሼክ መሐሙድ እና ከኬንያው ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ ጋር መወያየታቸውን በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው አስፍረዋል።

ብዙ የጋራ ጥቅሞቻችንን እና ሥጋቶቻችንን ከግምት ውስጥ በማስገባት የጋራ ተግዳሮቶቻችንን በድል ለመወጣት ኢትዮጵያ ከእያንዳንዱ ሀገር ጋር ተቀራርባ ትሠራለች ሲሉም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሁለቱ ሀገራት መሪዎች ጋር የመከሩት ከኢጋድ የመሪዎች ጉባዔ ጎን ለጎን መሆኑ ተገልጿል፡፡