የሀገር ውስጥ ዜና

ከ184 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ

By Mikias Ayele

June 12, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 5፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ከ184 ሚሊየን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ እቃዎች መያዙን የግምሩክ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ ቡና፣ መድሃኒት፣ ተሽከርካሪዎች፣ የጦር መሳሪያዎች፣ አደንዛዥ እጾች፣ እና የተለያዩ ሀገር ገንዘቦች ይገኙበታል፡፡

የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ በጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ በፌደራል ፖሊስ፣ በክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በብረራ እና ጥቆማ ነው የተያዙት፡፡

የኮንትሮባንድ እቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ ሶስት ግለሰቦች እና ሁለት  ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡