የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ዞን ከፍተኛ አመራሮች መድረክ በሱሉልታ ከተማ ተጀመረ

By ዮሐንስ ደርበው

June 13, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌደራል ዞን ከፍተኛ አመራሮች መድረክ በሱሉልታ ከተማ ተጀምሯል።

የብልጽግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከሰሞኑ ተወያይቶ ባስቀመጠው አቅጣጫ እንዲሁም በሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ላይ ውይይቱ ትኩረት ማድረጉ ተገልጿል።

መድረኩን የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ አባል አለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣አቶ አህመድ ሽዴ እና አቶ መላኩ አለበል የሚመሩት ሲሆን ከሁሉም ፌደራል ተቋማት የተውጣጡ አመራሮች ተሳታፊዎች መሆናቸውን የፓርቲው መረጃ ያመላክታል።

የውይይት መድረኩ መፍጠን እና መፍጠር ላይ ትኩረት በማድረግ ስኬታማ የብልፅግና ጉዞን ለማረጋገጥ አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ውስጣዊ አንድነቱን አጠናክሮ ጉዞ እንዲጀምር አቅም የሚገነባበት መድረክ እንደሚሆን ከወዲሁ ተገምቷል።