ዓለምአቀፋዊ ዜና

ቻይና ለአፍሪካ ቀንድ ሁለንተናዊ ሠላም እና ብልፅግና ድጋፍ እንደምታደርግ አስታወቀች

By Alemayehu Geremew

June 13, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 6 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ቻይና ለአፍሪካ ቀንድ ሠላም እና ብልፅግና ያላሰለሰ ድጋፍ እንደምታደርግ አረጋገጠች፡፡

የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) ዋና ፀሐፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) በአፍሪካ ቀንድ የቻይና ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ዡ ቢንግ ጋር ተወያይተዋል፡፡

አምባሳደር ዡ ቢንግ ÷ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ኢጋድን በድጋሚ ለማገልገል የመሪዎችን ጉባዔ እና የሀገራት መንግሥታትን የመተማመኛ ድምፅ በማግኘታቸው የተሠማቸውን ደስታ ገልጸውላቸዋል፡፡

አምባሳደሩ በትናንትናው ዕለት ጂቡቲ በተካሄደው 14ኛው የኢጋድ የመሪዎች እና የሀገራት መንግስታት መደበኛ ጉባዔ ላይ ባደረጉት ንግግር ÷ ኢጋድ በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና አድንቀዋል፡፡

በመልዕክታቸውም በቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች መምሪያ.ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዉ ፔንግ ቀጣናው የሠላም እና የብልጽግና ተምሳሌት እንዲሆን የሚደረገውን ጥረት ቻይና ትደግፋለች ማለታቸውን አረጋግጠዋል፡፡