የሀገር ውስጥ ዜና

አቶ ብናልፍ አንዷለም በስደተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዩጋንዳ ገቡ

By ዮሐንስ ደርበው

June 14, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር አቶ ብናልፍ አንዷለም የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት (ኢጋድ) እና የምስራቅ አፍሪካ ማህበረሰብ ተቋም (ኢ ኤ ሲ) በስደተኞች ጉዳይ ባዘጋጁት የሚኒስትሮች ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ዩጋንዳ ገብተዋል።

ኢንቴቤ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በዩጋንዳ የኢትዮጵያ አምባሳደር እፀገነት በዛብህ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

በስደተኞች ጉዳይ ላይ በተዘጋጀው የሚኒስትሮች ጉባኤ በባለሙያዎች ደረጃ ትናንት በዩጋንዳ መጀመሩ ይታወቃል።

ባለሙያዎቹ የመከሩባቸውን አጀንዳዎችም ለሚኒስትሮች ስብስባ ያቀርባሉ።