የሀገር ውስጥ ዜና

የግሪክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው ገለጹ

By Melaku Gedif

June 15, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 8፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ዳንኤል ተሬሳ ከግሪክ ባለሃብቶች ጋር በበይነ መረብ ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የግሪክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ በትኩረት መክረዋል፡፡

አቶ ዳንኤል የኢትዮጵያ እና ግሪክን የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲሁም የኢንቨስትመንት ትስስር ይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች በሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያም ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

የግሪክ ባለሃብቶች በበኩላቸው÷ በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን የማፍሰስ ፍላጎት እንዳላቸው መግለጻቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

በውይይቱ የአቴንስ የንግድ ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት እና የግሪክ የላኪዎች ማህበርን ጨምሮ ከ30 በላይ ባለሃብቶች ተሳትፈዋል፡፡