ዓለምአቀፋዊ ዜና

አሜሪካ ተጨማሪ ተዋጊ ጀቶችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ላከች

By Mikias Ayele

June 15, 2023

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አሜሪካ ተጨማሪ ተዋጊ ጀቶችን ወደ መካከለኛው ምስራቅ ቀጣና መላኳን አስታውቃለች፡፡

አሜሪካ÷ የሩሲያ ወታደራዊ አውሮፕላኖች በመካከለኛው ምስራቅ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መጨመሩን ተከትሎ ነው ኤፍ-22 የተሰኙ ተዋጊ ጀቶችን ወደ ቀጣናው የላከችው፡፡

ውሳኔው ሩሲያ በቀጣናው የምታካሄደውን ያልተፈቀደ ወታደራዊ እንቀስቃሴ ለመግታት እና የአሜሪካን ጦር አቅም ለማሳየት ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የፔንታገን ባለስልጣናት በቅርቡ ሞስኮ በሶሪያ በሚገኙ የአሜሪካ ጦር ሰፈሮች አካባቢ ያልተፈቀዱ በረራዎች አድርጋለች ሲሉ የወነጀሉ ሲሆን÷ አሁን ላይ ሩሲያ የምታደርገው መደበኛ ያልሆነ በረራ መጨመሩንም ጠቁመዋል፡፡

ሞስኮ በበኩሏ÷ ዋሽንግተን ቦሶሪያ ያልተፈቀደ በረራ እያደረገች መሆኑን እና አሁንም የሀገሪቱ  ጦር ከአሰራር ውጭ  በረራ እያደረገ ነው ስትል ወንጅላለች፡፡

አሜሪካ በአሁኑ ሰዓት በሶሪያ ውስጥ 900 የሚጠጉ እግረኛ ወታደሮች ያሏት ሲሆን÷ በአካባቢው የአየር ጦር ሰፈር እገነባች እንደምትገኝም አር ቲ ዘግቧል፡፡