አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 8 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሚዛን ከተማ 5 ሺህ 460 ግራም ወርቅ እና 130 ሺህ ብር ይዞ የተገኘ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ አስታወቀ።
ተጠርጣሪው በቁጥጥር ሥር መዋል የቻለው የማዕድን ግብይት አዋጅ ቁጥር 1144/2011 የደነገገውን ክልከላ ተላልፏል በሚል ነው፡፡
በዚህም ተጠርጣሪው በሕገ-ወጥ መንገድ የወርቅ ማዕድኑን በመኖሪያ ቤት በማስቀመጥ ለግል ጥቅሙ ለማዋል ሲል ፖሊስ ከኅብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በመኖሪያ ቤቱ ባደረገው ፍተሻ መሆኑን ከፌዴራል ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
የፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖራቸው በሕገ-ወጥ የማዕድን ግብይት ውስጥ በመሳተፍ ኢትዮጵያን ከማዕድን ዘርፉ የምታገኘውን ገቢ ለማሳጣት እየሠሩ ባሉት አንዳንድ ግለሰቦችና ቡድኖች ላይ ፖሊስ የጀመረውን ክትትልና ኦፕሬሽን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።
ህብረተሰቡ ማዕድናትን በጥቁር ገበያ የሚገበያዩ፣ በሕገ-ወጥ መንገድ የሚያከማቹ ግለሰቦችና ቡድኖችን በማጋለጥ አሳልፎ ለፀጥታ አካላት በመስጠት ኃላፊነቱን እንዲወጣም ፖሊስ ጥሪ አቅርቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!