የሀገር ውስጥ ዜና

“ፈጠራ በቀውስ ጊዜ” በሚል ርእስ የአዲስ ወግ ዌቢናር ተካሄደ

By Tibebu Kebede

April 28, 2020

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) “ፈጠራ በቀውስ ጊዜ” በሚል ርእስ የአዲስ ወግ ዌቢናር በቴክኖሎጂ በመታገዝ በቪዲዮ ኮንፍራንስ ተካሄደ።

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ሲዘጋጅ የቆየው የአዲስ ወግ አንድ ጉዳይ በቪዲዮ ኮንፍረንስ/ዌቢናር የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የሚያመጣውን ተከትሎ ለመጻዒ ፍላጎቶች እና ፈተናዎች ፈጠራ የታከለበት መፍትሔ ማፈላለግ ዙሪያ ትኩረቱን አድርጎ ምክክር አድርጓል።