የሀገር ውስጥ ዜና

ክልል አቀፍ የ2015 የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በሲዳማ ክልል ተጀመረ

By Alemayehu Geremew

June 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ)ክልል አቀፍ የአረንጓዴ ዐሻራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር “ነገን ዛሬ እንትከል” በሚል መሪ ሐሳብ በሲዳማ ክልል ዳራ ኦቲሊቾ ወረዳ ሾኢቾ ቀበሌ ተካሄደ፡፡

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሐመድ፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግሥት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ በልጅጌ፣ በብልጽግና ፓርቲ የሲዳማ ክልል ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አብርሃም ማርሻሎ እና በም/ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የኦሮሚያ ክልል የገጠር ክላስተር አስተባበሪ አብዱርሃማን አብደላ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገኝተዋል፡፡

በተጨማሪም የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ጀንበር (ዶ/ር)፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዮሐንስ ጫላ እንዲሁም የፌደራል እና የሲዳማ ክልል በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡

በብርሃኑ በጋሻው