አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) 28ኛው የኢትዮጵያ ሜዲካል ላቦራቶሪ ጉባዔ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡
ማህበሩ ከተመሰረተ ጊዜ ጀምሮ ሙያውን ለማሳደግና ለማሻሻል እየሰራ መሆኑ በመድረኩ ተገልጿል፡፡
ለሁለት ቀናት የሚቆየው ጉባዔው÷ የሕክምና ላቦራቶሪ ፖሊሲ ልማትና ትግበራ፣ የላቦራቶሪ አስተዳደር አቅምን ማጎልበት እና ሌሎችም ጉዳዮች ላይ ማተኮሩ ተመላክቷል፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የሜዲካል ላቦራቶሪው ዘርፍ ከተደራሽነት እና ከጥራት አንፃር ችግሮች ይታዩበታል ብለዋል፡፡
ለመፍትሄውም የግብዓት አቅርቦትን ጨምሮ ቀጣይነት ያለው ሥራ እየተሠራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በምንተስኖት ሙሉጌታ