የሀገር ውስጥ ዜና

በአዲስ አበባ ባጋጠመ የእሳት አደጋ 21 ሱቆች ወደሙ

By ዮሐንስ ደርበው

June 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 11 ሰፈራ አካባቢ በደረሰ የእሳት አደጋ 21 የንግድ ሱቆች መቃጠላቸውን የእሳትና አደጋ ስጋትሥራ አመራር ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

አደጋው የደረሰው ከጠዋቱ 1 ሰዓት ከ50 ደቂቃ መሆኑን የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ ንጋቱ ማሞ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡

በአደጋው የተቃጠሉት ሱቆችም የተለያየ የንግድ ሥራ የሚከናወባቸው መሆናውን ተናግረዋል፡፡

የእሳት አደጋውን ለመቆጣጠር 11 የእሳት አደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪና ሁለት የውሀ ቦቴዎች ከ70 የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ጋር መሠማራታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የንግድ ቤቶቹ የተገነቡበት ቁሳቁስና ቤቶቹ ተጠጋግተው መሰራታቸው እንዲሁም ለአደጋ ምክንያት የሚሆኑ አሰራሮች መኖራቸው የእሳት አደጋው በቀላሉ እንዲስፋፋ ምክንያት ሆኗል ብለዋል።

አደጋው ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳይደርስ መቆጣጠር መቻሉን እና ሥራውም 3 ሰዓት መውሰዱን አስገንዝበዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!