የሀገር ውስጥ ዜና

ሌ/ጄ ይልማ መርዳሳ ከአየር መንገዱ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገለፁ

By Meseret Awoke

June 16, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 9 ፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) አዲስ የተሾሙት የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉን ገለፁ፡፡

የኢፌዲሪ አየር ኃይል ዋና አዣዥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ከሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የቦርድ ሰብሳቢ ሆነው መሾማቸው ይታወቃል፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኞች ማህበር ለፋና ብሮድካስቲንግ በላከው መረጃ ፥ ሌተናል ጄኔራል ይልማ ከማህበሩ ሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ጋር በተለያዩ የጋራ እና ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በውይይቱ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ ÷ ከማህበሩ ጋር በጋራ ለመስራት ቁርጠኛ መሆናቸዉንና አስፈላጊዉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቀዳማዊ መሠረታዊ ሠራተኛ ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ኪያ ለማ በበኩላቸው ÷ ሌተናል ጄኔራል ይልማ መርዳሳ በአቪዬሽን ዘርፍ ያካበቱት የዳበረ የአመራር ልምድ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ መልካም እድል መሆኑን ገልጸዋል።

አቶ ኪያ ለማ አክለውም ፥ ከምንጊዜዉም በተሻለ ሁኔታ የሰራተኛዉን ጥቅም በማስከበር ረገድ ሰፊ ስራ እንደሚሰሩ ያላቸዉን እምነት በመግለጽ ማህበሩ አስፈላጊዉን ድጋፍ ሀሉ የሚሰጥ መሆኑን አረጋግጠዉ መልካምና ስኬታማ የሥራ ዘመን እንዲሆንላቸዉ ተመኝተዋል፡

ሌተናል ጀነራል ይልማ ፥ የሠራተኛ ማህበሩ እያደረገ ያለዉ እንቅስቃሴ የሚበረታታ መሆኑንና ወደፊትም የሠራተኛዉን ጥቅም ከማሳደግ አንጻር ከማህበሩ ጋር በበለጠ አብሮነት እንደሚሰሩ ተናግረዋል ፡፡

በተጨማሪም የተቋም ግንባታ ላይ በተጠናከረ መልኩ እንደሚሰሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!