የሀገር ውስጥ ዜና

የፊታችን ሰኞ በዎላይታ ዞን የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደት ይከናወናል

By Mikias Ayele

June 17, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 10፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በዎላይታ ዞን የፊታችን ሰኞ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ. ም. የሕዝበ ውሣኔ ምርጫ ድምፅ የመስጠት ሂደትን እንደሚያስፈጽም አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 12 ቀን 2015 ዓ.ም. በዎላይታ ዞን የሚያስፈጽመውን የድጋሚ ሕዝበ ውሣኔ ምርጫ የድምፅ መስጠት ቀንን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በዚህም መሠረት በዕለቱ የተመዘገቡ ዜጎች ሁሉ ድምፃቸውን መስጠት እንዲችሉ እንዲሁም የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ ያለምንም የፀጥታ ችግር እንዲከናወን ለማስቻል ቦርዱ የተለያዩ ተግባራት ተፈጻሚ እንዲሆኑ አሳስቧል፡፡

ተፈጻሚ የሚደረጉትን ጉዮችም የምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የሥነ ምግባር ዐዋጅ 1162/2011 አንቀጽ 161 የመተባበር ግዴታ መሠረት ቀጥለው የተጠቀሱት ጉዳዮች ተፈጻሚ እንዲሆኑ ለመንግሥታዊና ለማንኛውም መንግሥታዊ ላልሆኑ ተቋማት ማሳወቁን ቦርዱ ገልጿል፡፡