አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የአፍሪካ ህጻናት ቀን “ሰላም፣ ፍቅር፣ እንክብካቤና ጥበቃ ለሁሉም ህፃናት” በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ከተማ እየተከበረ ነው፡፡
የዘንድሮው የአፍሪካ ህጻናት ቀን በኢትዮጵያ ለ32ኛ ጊዜ ነው በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል በተለያዩ ዝጅቶች እየተከበረ የሚገኘው።
በመርሐ ግብሩ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)፣ የፓርላማ ተወካዮች፣ የፌዴራልና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ የህጻናት ፓርላማ ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
የዘንድሮው የአፍሪካ ህጻናት ቀን በአፍሪካ ደረጃ ለ33ኛ ጊዜ የአፍሪካ ህብረት በወሰነው መሰረት “የሕጻናት መብት በዲጅታሉ ምህዳር” በሚል አህጉራዊ መሪ ሃሳብ እንደሚከበር የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ሀገራት ህጻናትና የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ደህንነትን በተመለከተ በአፍሪካ የህጻናት መብቶችና ደህንነቶች ቻርተር ላይ የሰፈሩ ድንጋጌዎችን፣ ሌሎች ህጋዊ የአሰራር ማዕቀፎችን እና ሌሎች የአህጉሪቱን ነባራዊ ሁኔታ ታሳቢ ባደረገ መልኩ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ቀኑን አስበው እንደሚውሉ ተጠቁሟል፡፡