የሀገር ውስጥ ዜና

በሻሸመኔ በቆሻሻ ውስጥ የተጣለ ቦምብ ፈንድቶ የ4 ልጆች ህይወት አለፈ

By Feven Bishaw

June 19, 2023

አዲስ አበባ፣ሰኔ 12፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ ዛሬ ቆሻሻ ውስጥ ተጥሎ የነበረ ቦምብ ፈንድቶ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ የሚተዳደሩ አራት ልጆች ህይወት አለፈ፡፡

ልጆቹ ያገለገሉ ፕላስቲኮችን እየለቀሙ ባለበት ሰዓት ከተጠራቀመ ቆሻሻ ውስጥ ቦምቡ መፈንዳቱ ተመላክቷል፡፡

በዚህም የአራት ልጆች ህይወታቸው ሲያልፍ፥ ሁለት ህፃናት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡

ህይወታቸው ካለፈ ልጆች ውስጥ ሶስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት መሆናቸውን በከተማው የሀሩፋ ክፍለ ከተማ  የወንጀል ምርመራ ክፍል ኢንስፔክተር ከማል ጄይላን መግለፃቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ህፃናትም የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ታውቋል፡፡