የሀገር ውስጥ ዜና

ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የንግድ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

By Shambel Mihret

June 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ከእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የንግድ ሚኒስትር ኒገል ሃድልስተን ጋር ተወያይተዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታው ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) ÷በሁለቱ ሀገራት ያለውን የቆየ ወዳጅነት አንስተው÷ ስለተዘጋጀው ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ረቂቅ ላይ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የእንግሊዝ ዓለም አቀፍ የንግድ ሚኒስትር ኒገል ሃድልስተን በበኩላቸው÷የሀገራቸው መንግስት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የኢንቨስትመንትና የንግድ ግንኙነት ለማሳደግ ቁርጠኛ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡