የሀገር ውስጥ ዜና

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ  “ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርዕይ”ን  አስጀመሩ

By Shambel Mihret

June 20, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ “ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርዕይ”ን  ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም አስጀምረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ÷”ሀገር አቀፍ የጤና ዐውደ ርእይ” ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም አስጀምረናል ብለዋል።

በዐውደ ርዕዩ የመንግሥት እና የግል ተቋማት፣ በጤና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የተሠማሩ ድርጅቶች እንዲሁም የምርምር ተቋማት እንደሚሳተፉም ገልፀዋል፡፡