አዲስ አበባ፣ ሰኔ 13፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢፌዲሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በዛሬው ዕለት ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት(ዩኒዶ) ተወካይ ኦሬሊያ ካላብሮን ጋር ተወያይተዋል፡፡
ምክር ያደረጉት ፥ በኢትዮጵያ እና የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) መካከል ያለውን አጋርነት ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ነው።
አምባሳደር ምስጋኑ በዚህ ወቅት ፥ ኢትዮጵያ ከዩኒዶ ጋር በአግሮ ፕሮሰሲንግ ኢንዱስትሪዎች፣ በጨርቃ ጨርቅ፣ በቆዳና ቆዳ ውጤቶችና በፋርማሲዩቲካል ምርቶች ላይ አጋርነቷን ለማሳደግ ዝግጁ መሆኗን አረጋግጠዋል።
ተወካይ ኃላፊዋ ኦሬሊያ ካላብሮን በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ መንግስት እየወሰደ ያለውን የማሻሻያ እርምጃዎች አድንቀዋል፡፡
በተጨማሪም ፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅተ ኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት በኢትዮጵያ ለማከናወን ስላቀዳቸው ተግባራት ማብራራታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡