የሀገር ውስጥ ዜና

የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር ጋር ተወያዩ

By ዮሐንስ ደርበው

June 21, 2023

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 14፣ 2015 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በኢትዮጵያ ከቱርክ አምባሳደር በርክ ባራን ጋር ዛሬ ተወያይተዋል።

ቱርክ በትምህርት፣ በጤና እና ማህበራዊ ልማት እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፎች ድጋፍ በማድረግ እያከናወነች ላለው ስራ አቶ ኦርዲን አመስግነዋል፡፡

ሐረር ከተማ የጀጎል ግንብን ጨምሮ በዩኔስኮ የተመዘገቡ ዓለም አቀፍ ቅርሶች መገኛ መሆኗን አቶ ኦርዲን ገልጸዋል፡፡

በተጨማሪም የተለያዩ ባህል እና እምነት ያላቸው ህዝቦች በሰላም በፍቅርና በመቻቻል የሚኖሩባት ከተማ ስለመሆኗ መናገራቸውን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ መረጃ ያመላክታል፡፡

በቱርክ ከሚገኘው ሳንሉርፋ ከተማ ጋር እህትማማችነትን እና የህዝብ ለህዝብ ትስስር ለማጠናከር ይሰራል ብለዋል።

አምባሳደር በርክ ባራን በበኩላቸው÷ የኢትዮጵያ እና ቱርክ ግንኙነት ዘመናትን ያስቆጠረ እና በመልካም ወዳጅነት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያና ቱርክ ከፍተኛ የኢኮኖሚ አጋር መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!